ESIM Health Education የጤና ትምህርት
የስኳር ህመም መሰረታዊ ነገሮች (basics)
1. የስኳር ህመም ምንድር ነው?
2. የስኳር ህመም ስርጭት በአለም አቀፍና በአገራችን ደረጃ ምን ይመስላል?
3. ለመሆኑ የስኳር ህመም ስርጭት ለምን እየጨመረ መጣ?
4.ለስኳር ህመም አጋላጭ ሁሌታዎች ምንድር ናቸው? ሱስ የሚያስይዙ ልማዶችስ አጋላጭነታቸው ምን ያክል ነው?
5. የስኳር ህመምን አይነቶች ምን ምን ናቸው?
6.የስኳር ህመም ምልክቶች ምንድር ናቸው?
7. የስኳር ህመም ምርመራዎች ምንምን ናቸው?
8.የስኳር ህመም እንዴት ይታከማል?
9.የስኳር ህመምን ለመቆጣጠር የታካሚዉና የቤተሰቡ ሚና ምን መሆን አለበት?
10. የስኳር ህመም ተጓዳኝ የጤና ችግሮች ምንድር ናቸው?/

የኮሌስትሮል መድሃኒቶች ጠቀሜታ

የደም ኮሌስትሮል መጠን መጨመር የደም ስር ህመም የመያዝ እድልን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር በጥናቶች የተረጋገጠ ነው። በተለይም ኤል ዲ ኤል ኮሌስትሮል (LDL-cholesterol) የደም ስር ላይ የሚያስከትለው ጠንቅ አደገኛ ነው።
ኮሌትሮል የደም ስርን የሚጎዳው እንዴት ነው?
የደም ውስጥ ኮሌስትሮል መጠን ሲጨምር የደም ስር ግድግዳ ላይ በመጣበቅ የደም ስር ጤናን ያውካል። በጊዜ ሂደትም የደም ስር እያጠበበ የደም ዝውውርን ይገታል። ለአብዛኞቹ የአካል ክፍሎች ደም የሚያቀርቡትን ደም ወሳጅ የደም ቧንቧዎች ፍሰትን በመገደብ የልብ ድካም (heart attack)፣ የአንጎል መታወክ (stroke) እንዲሁም የእግር ህመም (gangrene) ያስከትላል።
የኮሌስቶርል መብዛት ምልክቶች ምንድር ናቸው?
ከፍተኛ ኮሌስትሮል ለብዙ ሰዎች ምንም ዓይነት ምልክቶች አያስከትልም። ከፍተኛ ኮሌስትሮል በሰውነትዎ ውስጥ ሌሎች ችግሮችን እስኪያመጣ ድረስ ምንም ዓይነት ምልክቶች አያሳይም። ምልክት አልባ ነው። ከፍተኛ ኮሌስትሮል እንዳለ ለማወቅ ብቸኛው መንገድ የደም ምርመራ በማድረግ ነው።
ህክምናዎቹ ምንድር ናቸው?
እንደ እድል ሆኖ በርካታ ውጤታማ የሕክምና አማራጮች አሉት።
ጤናማ የአኗኗር ዘዬ መከተል፣ በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲሁም አልኮል መጠጥ መቀነስ ለኮሌስትሮል ህክምና መሰረታዊ ናቸው። በተጨማሪም ከጤና ባለሙያዎ ጋር በመማከር የኮሌስትሮል መቀነሻ መድሃኒት ሊታዘዝ ይችላል። በተለይም የስኳር ህመም ያላቸው፣ የልብና ተያያዥ የደም ስር ህመም ያላቸው፣ የኮሌስትሮል መጠን በከፍትኛ ሁኒታ የጨመረባቸው እንዲሁም ተደራራቢ አጋላጭ ህመም (multiple risk factors) ያላቸው የኮሌስትሮል መቀነሻ መድሃኒት ያለማቋረጥ መውሰድ ተገቢ ነው።
ዋናዎቹ የኮሌስትሮል መቀነሻ መድሃኒቶች ስታቲን (statin) በመባል ይታወቃሉ። በርካታ የስታቲን መድሃኒት አይነቶች ቢኖሩም ኮሌስትሮልን በከፍተኛ ሁኔታ በማስተካከል ውጤታማነታቸው የተረጋገጠው ሮሱቫስታቲን (Rosuvastatin) እና አቶርቫስታቲን (Atorvastatin) የተባሉት የስታቲን መድሃኒቶች ናቸው።
ለተከታታይ የጤና መረጃዎች በድህረ ገጻችንና ማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉን
የታይሮይድ እጢ፣ እንቅርትና የታይሮይድ ካንሰር ምንድን ናቸው?
ያለግርታ ለመግባባት ያመቸን ዘንድ ከታይሮይድ እጢና ህመም ጋር ተያያዝ የሆኑ ቃላትን ስያሜ ወጥ የሆነ ትርጓሜ መስጠት አስፈላጊ ነው።
የታይሮይድ እጢ (thyroid gland)
የታይሮይድ እጢ በፊት ለፊተኛው የአንገታችን ክፍል ከማንቁርት ግርጌ የሚገኝ ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ ንጥረ ቅመሞችን (ሆርሞን) የሚያመርት የአካል ክፍላችን ነው።
በቅርጹ ቢራቢሮ መሳይ ሲሆን በአማካኝ ክብደቱ ከ20 እስከ 25 ግራም ይመዝናል።
የታይሮይድ ሆርሞን ዋና ዋና ተግባራት
• የሁሉንም የሰውነታችንን ህዋሳት ስራና መስተጋብር (metabolism) ይቆጣጠራል
• የሰውነት ሙቀትን ያስተካክላል
• ስርአተ እንሽርሽሪትንና የምግብ ውህደትን ያቀላጥፋል
• የአካላዊና አእምሮአዊ እድገትን ያሳልጣል
